This content requires Microsoft Silverlight.

Get Microsoft Silverlight

ምክር ቤቱ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የ500 ሺህ ብር ቦንድ ገዛ

ሚያዝያ 16 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚውል ከወለድ ነፃ የሆነ የ500 ሺህ ብር ቦንድ የገዛ ሲሆን በዛሬው ዕለት የርክክብ ስነ-ስርዓቱ በምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

የምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድና የማኔጅመንት አባላት ከወራት በፊት የግድቡ ግንባታ በሚከናወንበት በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ተገኝተው ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ጉብኝቱ በፈጠረው ከፍተኛ መነቃቃት በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት ቦርዱ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የ100,000 /መቶ ሺህ/ ብር የቦንድ ግዢ የፈፀመ ሲሆን የምክር ቤቱ ሰራተኞችና የማኔጅመንት አካላትም በ134,500 /አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሺህ አምስት መቶ/ ብር የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለቦንድ ግዢ ማዋላቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት 11 የክልልና የከተማ ምክር ቤቶች እና 7 የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች አባላቶቹን በመቀስቀስ በማደራጀት በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ለግድቡ ግንባታ የሚውል የቦንድ ግዢ እንዲፈፅሙ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ምክር ቤቱ የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ በተቻለው አቅም የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልፅ ነበር፡፡


7ኛው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው በግብር ይግባኝ አቀራረብ እና በቫት ተመላሽ አከፋፈል ያሉ ችግሮች ዙሪያ የምክክር መድረክ የግሉ ዘርፍና የመንግስት ተወካዮች በተገኙበት በደሳለኝ ሆቴል አዘጋጀ፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙሉ ሰሎሞን እንደተናገሩት ግብር መንግስትና ዜጎችን የሚያስተሳስር ሥርዓት እንደመሆኑ የተስተካከለ የግብር ሥርዓት የአንድ አገር የዲሞክራሲና የስልጣኔ ነፀብራቅ ነው ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የምክር ቤቱ አመራሮች ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር መከሩ

ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር የግል ዘርፉን ለማጠናከር እየተደረጉ ባሉት ጥረቶች ዙሪያ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሊኖረው ስለሚችለው ሚና ላይ ተወያዩ፡፡

የምክር ቤቱ አመራሮች ፕሬዚዳንት ሙላቱ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እንዲሁም የግል ዘርፉን አቅም ለማሳደግ እያከናወኑዋቸው ያሉትን ተግባራት እንደሚያደንቁ በመግለፅ ምክር ቤቱና የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት የግል ዘርፉን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት በጋራ ሊሰሩባቸው ይችላሉ ያሉዋላቸውን አራት ዓበይት ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን እነዚህም በዐቅም ግንባታ ዙሪያ፤ ከተለያዩ ሃገራት ኤምባሲዎችና ምክር ቤቶች ጋር የጠነከረ ግንኙነት በመፍጠር ረገድ፤ መልካም ሥነ ምግባርና ኮርፖሬት ሃላፊነትን ከማጎልበት እና የፈጠራ ውጤትን ከማበረታታት አኳያ የሚደረጉ ድጋፎች የሚሉ ናቸው፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የኢትዮጵያና የኬንያ የንግድ ልዑካን የአቻ ለአቻ ውይይት አካሄዱ

የሁለቱ አገራት ምክር ቤቶች የመግባቢያ ሰነድ ፈረመዋል

የኢትዮጵያና የኬንያ የንግድ ልዑካንን በአንድ ላይ ያሰባሰበ የሁለትዮች የንግድ ፎረምና የአቻ ለአቻ ውይይት መጋቢት 4 ቀን 2006ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የኬንያው ፕሬዚዳንት ሚስተር ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ ከፍተኛ የሁለቱ ሀገራት የመንግስት ባለስልጣናት፣ ሚንስትሮች፣ የሁለቱ ሀገራት አምባሳደሮች እንዲሁም ከፍተኛ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት በተገኙበት የተካሄደው የአቻ ለአቻ ፎረም ሁለቱ ሀገሮች በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በሌሎች መስኮች የጀመሩትን ግንኙነት አጠናክረው ለመቀጠል የተስማሙበትና በርካታ ውሳኔዎች የተላለፉበት መድረክ ሆኖ አልፏል፡፡ ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የምክር ቤቱ አመራር አካላት ከጀርመን ሬማን ፕሮጀክት ኃላፊዎች ጋር መከሩ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድና የማኔጅመንት አባላት ከጀርመን ሬማን ፍራንክፈርት (HWK) እና ከጀርመን የንግድ ምክር ቤት የሥራ አመራርና የአማካሪ ቡድን ከምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ከማኔጅመንት አካለት ጋር መከሩ፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የዱባይ የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ተወያዩ

በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኢኮኖሚ ሚንስትር ክቡር ኢንጂነር ሱልጣን አልመንሱር የተመራ ከፍተኛ የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት አደረጉ፡፡ በሸራተን ሆቴል መጋቢት 9 ቀን 2006ዓ.ም. በተደረገውን የኢትዮ-አረብ ሜሬትስ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ሚንስትሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ በቅዱስ ቁራን ከፍተኛ ስፍራ ካገኙ የዓለም ሀገራት አንዷ መሆኗን አውስተው የመጀመሪያው ኢስላም ንጉስ የነጃሺ ሀገር ጭምር በመሆኗም በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ዘንድ ከፍተኛ ክብር እንደሚሰጣት ገልፀዋል፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የጣሊያን የንግድ ልዑካን ቡድን ከምክር ቤቱ አመራሮች ጋር ተወያየ

የጣሊያን የንግድ ልዑካን ቡድን እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አመራሮች በሁለቱም ሃገራት ስላለው የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሁኔታና ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉት ሠፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ላይ ተወያዩ፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የምክር ቤቱ የማኔጅመንት አባላት በቅርብ ከተሾሙ አምባሳደሮች ጋር መከሩ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ አቶ ጋሻው ደበበና ምክትላቸው አቶ እንዳልካቸው ስሜ ከሌሎች የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን አዲስ ከተሾሙ ሁለት አምባሳደሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የቻይና የንግድ ልዑካን በመጋቢት ወር መጨረሻ ሊመጡ ነው

ቁጥራቸው ከ20 እስከ 25 የሚጠጉ የቻይና የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት ለማድረግ እና እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማየት በመጋቢት ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የቻይና የሳይንስና ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ልዑክ ሚስ ኩንግ ዚያ ገለፁ፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ የጫኑ


የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ የባህል ዘርፍን ለማጠናከር 10 ሚሊዮን ዩሮ (260 ሚሊዮን ብር) ለገሰ

የካቲት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየን በተከናወነው ስነ ስርዓት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር አቶ አሚን አብድልቃድር እንደገለፁት መንግስት ለባህልና ቱሪዝም ዘርፍ እድገት ከመቼውም በላይ ትኩረት የሰጠ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ዛሬ ያደረገው ልገሳ ይህንን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


የቱሪዝም መዳረሻዎችን አቅም ለማጎልበት ጥረቱ ሊቀጥል ይገባል

ኢትዮጵያ የብዙ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት መሆኗ ተደጋግሞ ቢነገርም ዛሬ በርካታ የዓለም ሀገራት በዋናነት ከቱሪዝም ከሚገኝ ገቢ ከፍተኛ ገቢ ማግባት የቻሉበት ደረጃ ላይ ሲሆኑ ሀገራችን በአንፃሩ ወደ ኋላ መቅረቷ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ለጥቂቶች ደግሞ የሚያስቆጭ ነው፡፡ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘርፉን ለማሳደግ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡ ፡ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ ድርጅቶች ከመንግስት ጋር በመሆን እያደረጉ ያሉት ድጋፍ ለዘርፉ እድገት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ልዩነት መፍጠር ችሏል፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ


ምክር ቤቱና አ.አ.ዩ. የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአቅም ግንባታ፣ በምርምርና በመሳሰሉት ዐበይት ጉዳዮች ዙሪያ በጥምረት ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ጥር 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ፈረሙ፡፡ECCSA e-Newsletter ያንብቡ

ሂደቱን የሚያሳያ ፎቶዎች ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

ECCSA procures additional bond worth 500, 000 birr, interest free

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) procured bond for the construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) with an outlay of 500 thousand, interest free.

The handing over ceremony of the Bond certificate was conducted today at the ECCSA auditorium, where representatives from the GERD mobilization office, Madam Mulu Solomon, president of the ECCSA, Board of Directors of the ECCSA, members of various media, and management staff of the ECCSA were in attendance.

Handing over the certificate, Madam Mulu said, “The visit paid by the board in the construction site of the GERD was a moment in time to remember where nationalistic feeling was igniting among us, which caused procurement of additional bond by the ECCSA.”

Assuring that ECCSA would continue to back until the construction of the GERD is realized, Mulu said, “we will not stop after the completion of the GERD. We will also start another one.”

Representative of the office of the GERD project mobilization on his part said that it is my best conviction that the ECCSA could contribute a lot towards mobilizing and sensitizing the public towards one national agenda; in this case towards the construction of the GERD.

The Board of Directors of the ECCSA passed the decision following the visit by the board and the management in the actual construction site of the project, Guba woreda of Metekel Zone, Benishangul Gumz regional state located some 900 kilometers from Addis Ababa.

It is recalled that the ECCSA has previously procured a bond with an outlay of 100,000 birr; in addition to what the employees and the management contributed their monthly salary, amounting 134,500 birr.

ECCSA is devising a formula on to how to mobilize the business community at large through its 11 member chambers and 7 sectoral associations, it was learn.


Newly Appointed Ambassadors confer with ECCSA Secretariat

By Eyob Tadelle

The newly appointed ambassadors of Turkey and Brazil, Ayalew Gobeze and Sinkinesh Ejigu respectively discussed with management of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), led by the Secretary General Gashaw Debebe, on various issues of mutual interest. On the occasion held at ECCSA’s auditorium, the two ambassadors sought major activities of the chamber for which the Secretary General elaborated the missions, visions and core activities of that the chamber has been doing since its establishment 66 years ago. ...Read More


Chamber Officials Visit Ayka Addis Textile Factory

Officials of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations visited Ayka Addis Textile & Investment Group (AATIG), the Company’s headquarters located in Alemgena – a town located in the Oromia Regional State. Officials of the Chamber led by President Mulu Solomon also held discussions with the owner and Manager of the Factory Mr. Yusuf on the overall functioning of the textile factory. The Manager raised some challenges associated with human resource such as huge turnover of employees, problems related with industrial peace, discipline and ethics at work, among others. The President expressed her gratitude for the warm welcome offered to the chamber officials by the management of the Company. Mulu also said that the national chamber would do its level best to help redress the challenges that the factory is facing...Read More


Secretary General lauds HwK ECCSA Partnership Project

By Eyob Tadelle

Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations lauded the HwK-ECCSA Partnership project, which he described it as ‘one of the most successful projects’ in building the capacity of members of the national chamber.

The Secretary General made the remark while discussing with members of the Handwerkskammer Frankfurt- Rhein-Main on the overall performance of the Hwk-ECCSA Partnership project, possible ways of extension and other issues. Gashaw explained the main roles of the national chamber as trade and investment promotion, advocacy and capacity building. He said that the ECCSA has been working to create a strong private sector in the country in collaboration with other stakeholders and development partners.

The Secretary General said that the Hwk-ECCSA has been instrumental in building the capacity of member chambers and it is one of the most successful projects that the ECCSA has been undertaking in collaboration with its partners. Gashaw requested for the extension of the project given the paramount importance it has been playing in building the capacity of its members and strengthening the chamber system.

Representatives of the Frankfurt- Rhein-Main on their part said that they are delighted for the project is being well implemented and helping the Ethiopian chamber system. The representatives said: “though the discretion of extension is of the German government, there is high possibility of extension.”


Chamber Officials host Italian Business Delegation

Ethiopia’s relation with Italy goes far back in history. It is associated with the long history of Ethiopia and Europe. In the same vein, Italian diplomatic and political links with Ethiopia continued in the 19th and 20th centuries via diplomatic, commercial, colonial and modernization links. Italians were also closely associated with the creation of a modern Ethiopian state from the 1930s onwards. After 1991, however, Ethio–Italy relationships have been significantly changed to accommodate diplomatic, economic, trade and investment partnerships. Ethiopia’s relations with Italia are now far more solid than ever before.


HwK-ECCSA Partnership Project Organizes Various Capacity Building Trainings

The Hwk-ECCSA Partnership Project organized trainings on trade show organization, good governance and human resource development to members of the national chamber, regional as well as city chambers. Opening the trainings, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Gashaw Debebe said that the Hwk has been supporting the national chamber on various areas such as on trade and investment promotion, capacity building and advocacy. To this end, Gashaw said, the project has helped the chambers to build their capacities in particular and the chamber system in general.


Follow Us:


Visitors Since 2013Web Counter


ECCSA's BDS Publications


ECCSA's Members

Large